“ሮላንድ ፈሳሙ” (Roland the Fartter)
የምዕራቡ ዓለም የቀልድ ምንጭ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ነገሮች አንዱ የዓየር ማምለጥ ( ፈስ ) አንዱ ነው ብል እንደ ነውር አይቆጠርብኝ። ይህ የቀልድ ዓይነት በጣም ታዋቂ ከመሆኑ የተነሳ ለነገስታት ለመሳፍንት፣ ለመኩዋንንት በመድረክ ላይ ይቀርብ ነበረ። ቀጥሎ የምታነቡት ጽሁፍም በግጥም መልክ የቀረብ “ የሮላንድ ፈሳሙ ” እውነተኛ ታሪክ ነው። ሮላንድ የተደነቅበት ልዩ ችሎታው ሶስት ነገሮችን፣ ማለትም በላቲን ቋንቋ: “Unum saltum et siffletum et unum bumbulum.” በእንግልዝኛው : “One jump, one whistle, and one fart” አቀነባብሮ በአንድ ጊዜ በማሰማት ነበር። “ ሮላንድ ፈሳሙ ” አምባቢ መልካም ሰው ጉድ ልንገርህ እንካ ለንጉስ ያገሳም ለንጉስ የፈሳም ይሸለማል ለካ! ነገሩ አንዲህ ነው በል እንግድህ አድምጥ፤ “አንድ ዙጥ ወይም አንድ ዛጥ አንድ ፉጨት እና አንድ እንጣጥ” የሚተገብር በአንድ ጊዜ እያነባበረ በዚህ ችሎታውም ተሹሞ የከበረ የችሎት አጫዋች ንጉስን በሳቅ ያሰከረ እሱ ተዋርዶ ሳቅ ያመነጨ የነጋሲን ሃዘን ባጭር የቀጨ ድንቅ ስራውን መኩዋንትና ወይዛዝርት የመሰከረ ዝናው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በሰፊው የተነገረ በሔንሪ ዳግማዊ ዘመን ተከብሮ የኖረ “ ሮላንድ ፈሳሙ ” የሚባል ድንቅ ባለ ሙያ - ፈሳም ነበረ። *** ታድያ እንደ ልማዱ የገና በዓል ማሳረግያ ዕለት ንጉሱና ንግስቲቱ መሳፍንቱ መኳንንቱ ወይዛዝርቱ በተገኙበት ሮላንድ እንደልማዱ፥ “አንድ ዙጥ ወይም