“ሮላንድ ፈሳሙ” (Roland the Fartter)
የምዕራቡ ዓለም የቀልድ ምንጭ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ነገሮች አንዱ የዓየር ማምለጥ (ፈስ) አንዱ ነው ብል እንደ ነውር አይቆጠርብኝ። ይህ የቀልድ ዓይነት በጣም ታዋቂ ከመሆኑ የተነሳ ለነገስታት ለመሳፍንት፣ ለመኩዋንንት በመድረክ ላይ ይቀርብ ነበረ። ቀጥሎ የምታነቡት ጽሁፍም በግጥም መልክ የቀረብ “የሮላንድ ፈሳሙ” እውነተኛ ታሪክ ነው። ሮላንድ የተደነቅበት ልዩ ችሎታው ሶስት ነገሮችን፣ ማለትም በላቲን ቋንቋ: “Unum saltum et siffletum et unum bumbulum.” በእንግልዝኛው: “One jump, one whistle, and one
fart” አቀነባብሮ በአንድ ጊዜ በማሰማት ነበር።
“ሮላንድ ፈሳሙ”
አምባቢ መልካም ሰው ጉድ ልንገርህ እንካ
ለንጉስ ያገሳም ለንጉስ የፈሳም ይሸለማል ለካ!
ነገሩ አንዲህ
ነው በል
እንግድህ አድምጥ፤
“አንድ ዙጥ ወይም
አንድ ዛጥ
አንድ ፉጨት
እና አንድ
እንጣጥ”
የሚተገብር በአንድ
ጊዜ እያነባበረ
በዚህ ችሎታውም
ተሹሞ የከበረ
የችሎት አጫዋች
ንጉስን በሳቅ ያሰከረ
እሱ ተዋርዶ ሳቅ ያመነጨ
የነጋሲን ሃዘን
ባጭር የቀጨ
ድንቅ ስራውን
መኩዋንትና ወይዛዝርት የመሰከረ
ዝናው ከጽንፍ
እስከ ጽንፍ በሰፊው
የተነገረ
በሔንሪ ዳግማዊ ዘመን ተከብሮ
የኖረ
“ሮላንድ ፈሳሙ”
የሚባል ድንቅ ባለ
ሙያ-ፈሳም
ነበረ።
***
ታድያ እንደ ልማዱ የገና በዓል ማሳረግያ ዕለት
ንጉሱና ንግስቲቱ መሳፍንቱ መኳንንቱ ወይዛዝርቱ በተገኙበት
ሮላንድ እንደልማዱ፥ “አንድ ዙጥ ወይም አንድ ዛጥ
አንድ ፉጨት እና አንድ እንጣጥ”
አንዱ ሳይቀድም ሌላው ሳይዘግይ
አንዱ ከሌላው በጊዜ ሳይለይ
በሙዚቃ ፋንፋር በከበሮ ድምድም እየታጀበ
የፈስ ትርዕቱን ለታዳሚዎቹ በመድረክ ላይ እንዳአቀረበ
ታዳሚ ሁሉ በደስታ ሲቃ አጨበጨበ።
የሁሉም ስሜት
በደስታ ጋለ በደስታ
ፈካ
ሰው ፈነደቀ
በሳቅ አሽካካ፣
መድረክ ላይ
ማግሳትም፣ መድረክ ላይ
መፍሳትም ያስደንቃል ለካ!
ሔንሪ ዳግማዊ
አጅግ ፈነጠዙ
ቀደም ሲል
እንዳል ተከዙ
ከያኒው ለዚህ ሙያው
እንዲሸለም አዘዙ።
የንጉሱ ትዕዛዝም
ውሎ አድሮ
ተፈጸመ
ሮላንድ አንድ
ትልቅ
ህንጻና ሁለት ጋሻ
መሬት ተሸለመ
“የአንድ ዙጥ ወይም
የአንድ ዛጥ
የአንድ ፉጨት እና
የአንድ እንጣጥ”
ቅንብርን አሳምሮ ስለተለመ
በመድረክ ላይ
አሳክቶ ስለፈጸመ
ሮላንድ ህንጻና ርስት ተሸለመ።
በርግጥ የጃንሆይ ውሳኔ አስክትሎ ነበር ትችትና ወቀሳ
በአንድ ወገን፣ “ርስት ይሸለማል ወይ አንድ ሰው በመድረክ ላይ ስለፈሳ”
በሌላ ወገን፣ “እንዴ! ማን አለ ለጃንሆይ ደስታ ሲል መድረክ ላይ የማይፈሳ?”
ሶስተኛው ወገን ደግሞ ሶስተኛ ሃሳብ ሰነዘረ
“በመሰረቱ አዲስ ነገር የለም ነገርን ነገር ካላከረረ
በመድረክ ላይ እየፈሱ ርስትና ህንጻ መሸለም ባህላችን ነው የከበረ
አሁንም ያለ፣ ወደፊትም የሚኖር፣ ጥንትም የነበረ”
የሚል ጥያቄና ውዝግብ፣ ትችትና ጉምጉምታ አስሰነዘረ።
ሆኖም ጃንሆይ ዳግማዊ በመድረክ ላይ እያስፈሱ
ርስትና ህንጻ እየለገሱ
ጥቂት ዓመታት እንደነገሱ
ሞተው ስልጣናቸውን በሌላ ንጉስ ተወረሱ።
ከዚያም ሔነሪ ዳግማዊ እንደ ሞቱ
በሔነሪ ሳልሳዊ ስም ተቀብተው የነገሱቱ
ይህ ሽልማት ለሮላንድ አይገባውም ብለው ሞገቱ፣
ያለፈውን ንጉስ እያብጠለጠሉ
በመድረክ ላይ እየፈሱ ርስትና ህንጻ መቀበሉ
አይገባም፣ “indecent” ነው አሉ።
“ሮላንድ ፈሳሙ” በሙያው ጎልቶ እንዳልታውቀ
በክህነተ ሙያው የረቀቀ የመጠቀ
ከማንም ተራ ፈሳም በልጦ አንዳላቀ
በንጉስ፣ በምሳፍንት በመኩዋንንት እንዳልተደነቀ
ጥሮ፣ግሮ፣ ለፍቶ፣ ፈስቶ ያገኘውን ርስት ተነጠቀ።
ለካ አባት የሾመውን ልጅ መሻሩ ድሮም ነበረ
“ሮላንድ ፈሳሙ” በሔንሪ ዳግማዊ እንዳልከበረ
በሔነሪ ሳልሳዊ ርስትና ቤቱ ተወረሰና ከሰረ።
እናም…..
በመድረክ ላይ እየፈሳ ርስት ሊሸለም አኮብኩቦ የከረመ
ይህ ድንቅ ባህል መቁዋረጡን በዉስጡ ተቃወመ
በአፉ እያግተመተመ ሔነሪ ሳልሳዊን በልቡ ረገመ
በመድረክ ላይ እየፈሱ ርስት መሸለምም ለጊዜው አከተመ።
ዘለዓለም አበራ ተስፋ
01.
02. 2022
ሔልሲንኪ/ፊንላንድ
Comments
Post a Comment