Posts

Showing posts from August, 2021
  እይታ ለግሌ                                           ዘለዓለም አበራ ተስፋ                                                         11.07.2021    ለሰው ማዬት ቢሰለቸኝ ለግልዬ አዬሁልኝ አየሁልኝ ብዙ ነገር የተፈጥሮን ድንቅ ምስጥር ተረተሩ ሲተረተር ወናፍ አየር ምጎ ሲወጠር ኘስስስ ሲል … ተፍቶ አየር ፍቅር ጥላቻን ሲያመር ጥላቻ ፍቅርን ሲያመር ቁንጫ ቁንጭትን ሲሰር ትንኝ   ትንኝትን ሲያበር ሸረሪት ድሩን ሲያከር፣ አስመሳይ የሌሊት ወፍ ከወፎች ጋር እንደ ወፍ ክንፉን ዘርግቶ ሲከንፍ ካይጦችም ዋሻ ሲወተፍ የስጋ ዝምድና ሊቀፍ አየሁ፣ መቼም ዓይን አያርፍ፣ ያኛው ሲሔድ ይህ ሲመጣ ከፍ አልኩ ሲል ሲቀናጣ ሲንጠለጠል እንደ ቋንጣ ከላይ ሆኖ ስም ሲያወጣ ስም አለቀ ከዬት ያምጣ ለሱ የሚሆን ስም እስኪታጣ አቦ ስንቱን አየሁ አቤት ጣጣ፣ የሰው አንጆ እርጥብ ስጋ ለሁሉ ኣድር ባይ የሰው መንጋ እነሳቸው አ አክ ሲሉ የሚንጋጋ እንዲተፉበት የጅ መዳፉን የሚዘረጋ የመቤቱ ውታፍ ነቃይ ለጌቶቹም ታማኝ ነኝ ባይ ወሸከሬ የሰው አውደልዳይ በሳሎንም ባደባባይ፣ ኧረ ስንቱን አዬሁ በግላጭ አይጠ-ሞገጥ ከቋጥኝ ሲጋጭ በቂጡ ወድቆ   ሲንዘጭ ባለቅኔው ሲቀነቅን ሲቀኝ ባላንጣዬ   እንድጨልም ሲመኝ እምቢ ብዬ በራሁልኝ ። “የዳመና አመልማሎ ከሰማይ ዳገት ተንከባሎ ሲጠጥር እንደ አሎሎ ሲንከራተት ውሃ አዝሎ በምላሰ-ጣት ተፈትሎ ለታረዘ ሁሉ ቡልኮ” ሆነ በል ይለኛል እኮ! ከዝያማ…..“አገር ምድሩን እያለበሰ ጅረት ሆኖ ሞልቶ ፈሰሰ” ብለህ በል ሲለኝ እምቢ አ