……. አለ ዲጋ ሳቆ!
……. አለ ዲጋ ሳቆ ! ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ “ ኮርማ ባጣ አንገት አላጣ ” ! አለ ዲጋ ሳቆ የጆቴ አባት መታያ እውነትን የገደለ ዕለት ፤ “ ኮርማ ባጣ አንገት አላጣ ” ! አለ ዲጋ ሳቆ የኖሌ አባት ያገር ዳኞች የዋሹ ዕለት ፤ “ የሲቃ ዕለት ፤ … የእልህ ቀን እኔው ነኝ ኮርማ ፤ … እኔው ነኝ ወይፈን ”! አለ ዲጋ ሳቆ የጆርጎው ሰው የሱ እልሁ እኩያ የለው ። *** መዳፍ ታክል ትንሽ ኩሬ ለከብት ሆራ ለሰው አውሬ መሀል ድንበር ተ ሸንቁራ የምትገኝ ያም የኔ ናት ፤ ያም የኔ ናት ፤ የምታሰኝ ወይ ለዚህኛው ወይ ለዚያኛው ያልተገባች የእገሌ ሆራ ያልተባለች የጸብ መንስኤ የነገር ምንጭ ህዝብ አዋኪ አገር በጥባጭ ሰላም ነስታ እያወከች ሁለት ሞቲ ታፋጃለች። ነጋ ጠባ፤ ዓመት ካመት ሁለት ሞቲ እንደ ጠላት አይናገር፤ አይወያይ፤ አይዋደድ ሆኖ ይኖራል ጀርባና ሆድ። *** ይህ ነገር እንዲቆረጥ ጠቡ እንዲፈርስ ሰላም ሰፍኖ ፍቅር እንዲነግስ እውነት ከመንበሩ እንዲመለስ ሞቲዎቹ እንዲታረቁ ያገር ዳኞች የታወቁ ከባ...